ሰላም ይዲዲያና ትንሳኤ ነን፤ ሁሌም ሀሳቦችን እያነሳን የምንጫወትና የምንሟገት፥ ያወቅነውንም በቻልነው መጠን ለመኖር የምንጥር ጓደኛሞች። በዚህ ፖድካስት ከሕይወት ዋና ጥያቄዎች መሃከል እንደ ማንነት? “እንዴት ትርጉምና ዓላማ ያለው ኑሮ መኖር ይቻላል?” ከሚለው እስከ “ቲማቲም ፍሩት ከሆነ፥ ካችአፕ ጁስ ነው እንዴ?” እስከሚሉት ጥያቄዎች ይነሳሉ። ምን አለፋቹ ከገደብ ውጭ የሆነ ጥያቄ የለም። መልስ ላይኖረን ይችላል ነገር ግን ሁልጊዜም ጠብታ ሃሳብ እንደሚኖረን እርግጠኞች ነን። ስለዚህ የዚህ ሃሳቦችን የመመርመር ጉዞአችንን እንድትቀላቀሉ እንጋብዛችኋለን። ጠብታ ሀሳብ ይውሰዱ፤ ጠብታ ሀሳብ ያቅርቡ፤ ሞገዱን ይቀላቀሉ።
All rights reserved.
Sign up to track rankings and reviews from Spotify, Apple Podcasts and more.